ላገልግለው /4/
ላገልግለው ከትላቱ ይልቅ
እኔ ደስ ይለኛል እግ/ር ሲተልቅ /2/
ላመስግነው ከትላንቱ ይልቅ
እንዴት ደስ ያሰኛል እግ/ር ሲተልቅ /2/
ከፊት ለፊቱ ቆሜ በመዝሙሬ ሳመልከው
ገጽታውን እያየው በደስታ እሞላለሁ
ኖሬስ አይጓደለው ሳይነሳ አምላኬ
አከብረዋለሁ ገና /2/ መች አበቃሁ ተርኬ
አካላቴ ንቁዎቹ ለሱ እንዴት ይዝላሉ
መታደል ነው ማመስገን እግ/ር ይላሉ
በከበሮ ውብ ዜማ በሽብሸባ ተዋዝቶ
ዛሬም ልዘምርለት ልቤ በትላንቱ መች እረክቶ
እስኪ ጊዜው አትለፍ እግ/ር ሳልጠራ
አላውቅም ሌላ ደስታ እኔ ይህን ሳልሰራ
ዛሬ አዲስን ነገር ይኸው ይቼለታለሁ
አቤት ደስታውን ሳስብ ሐሴት አረጋለው እረካለሁ
