እንከን የሌለበት

91

እንከን የሌለበት የምስጋና ሽታ
ለታላቅነትህ ይገባሃል ጌታ
ሁሉም ያሞጋግስህ ባመረ ምስጋና
ሁሌ ልትወደስ ይገባሃልና

ያለምክንያት ክበር ጌታ ያለልክ
ፍጥረት ያዚሙልህ ስምህ ይባረክ
ምላሶች ያዚሙ ለአንተ ዝም ኣይበሉ
ከፍ በል ተወደስ ሁልጌዜ ይበሉ

ምስጋና ለአንተ ይገባሐልና
ዝማሬ ለአንተ ይገባሐልና
አምልኮ ለአንተ ይገባሐልና ጌታ
ውለታህ ከአይምሮ በላይ ነውና ተባረክ
ዙፋንህ ይሙላው ምስጋና
ተመለክ መንግስትህ ይሙላው ምስጋና ጌታ

አንተ መጠጊያ ነህ አንተ ምርኩዝ ነህ
መች ተስፋው ሊጨልም የሚደግፍህ

ጉልበትህ አይዝልም ታስተማምናለህ
ኣቤት የኛ እግ/ር እንዴት
ድንቅ አምላክ ነህ

ያርግ አይቁም ይዝነብ ምስጋና በቤትህ
በሰማይ መኖሪያህ ባደባባዬችህ
አንተን ደስ ይበልህ እኛ አንዘምራለን
ሁል ጊዜ ተመስገን ተመስገን እያልን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top