እግዚአብሔር በዙፋኑ ላይ ነው /3/
ይሰራል ዛሬም እርሱ ህያው ነው /3/
የበአል ነቢያት ቁጥራቸው ቢበዛም
የሚጠሩት አምላክ ግዑዝ ነው አይሰማም
የኤልያስ አምላክ አለ በዙፋኑ
በእሳት የሚመልስ ታማኝ ነው እንደቃሉ
ታምነን እንጠራዋለን
መቼም እርሱ አያሳፍረን 2x.
ሀይሉን ክብሩን እናያለን
ከግብፅ የወጣነው እርሱን ተማምነን ነው
አሁንም እግዚአብሄር እርሱ ሀይላችን ነው
ዮርዳኖስ ቢሞላም ቢገታም ጉዟችን
ታምረኛው አምላክ አለ ከጎናችን
በእርሱ እንታመናለን
በጌታ እንታመናለን
በኢየሱስ እንታመናለን
የፈርኦን ሰራዊት የእሳት ሰረገላ
አያስጨንቀንም ጌታ አለ ከእኛ ጋር
ዛሬ ያየናቸውን ዳግም ላናያቸው
ቀይባህር ሰጠሙ ከፈረሳቸው
ካለ የእስራኤል ታዳጊ
ካለ የእስራኤል ተዋጊ
ማነው ከቶ ለእኛ አስጊ
