አቤቱ አቤቱ
አንተ ያለህለት በሕይወቱ
በሌላም አይቀና በፊቱ
ተማምኖ ይኖራል በቤቱ
ካንተ ጋራ በዳገት በሜዳ
ካንተ ጋራ መፍትሔ ነህ ሚረዳ
ካንተ ጋራ አረፈ ምኞቱ
ካንተ ጋራ ፍቅር ሞላ ቤቱ
አቤቱ ……
ካንተ ጋራ ከዓለም እርቆ
ካንተ ጋራ ካንተ ጋረ ተጣብቆ
ካንተ ጋራ የሰው መጨረሻው
ካንተ ጋራ አማረ መድረሻው
አቤቱ ….
ከሱ ጋራ የዘላለም ጉዞ
ከሱ ጋራ እ/ርን ይዞ
ከሱ ጋራ ከቶ አይጐል ከቋቱ
ከሱጋራ ብዙ ነው ባርኮቱ
አቤቱ ……
ምንም ባይኖረው እግዚአብሔር ያለኸው
ሃሴት ያደርጋል በፀጋህ ሸፍነኸው
ሌላ ባይኖረው እግዚአብሔር ያለኸው
ረክቶ ይኖራል የነፍስ ዕረፍት ሆነኸው
የኔ የሚለው ዘመድ ወዳጅ ባይኖረው
ሙሉ ይሆናል እግዚአብሔር ያለኸው
እግዚአብሔር ያለኸው /2/
ሁሉ ያለህ ያለኸው
ያ ምስጉን ሕዝብ ነው
እግዚአብሔር ያለኸው /2/
ሁሉ ያለህ ያለኸው
ስራው ምስክር ነው
ዕረፍቱ ብዙ ነው
ሰላሙ ብዙ ነው
ዕድሉ ያማረ ነው
