እኔ እወድሃለው ኢየሱሴ
አመልክሃለው ገና ንጉሤ
እኔ አንተን ብያለሁ ህይወቴን ልሰጥህ
አመሰግናለሁ ጌታ ምን ልበልህ
ኢየሱስ/2/ እኔ አንተን ብያለሁ
አገለግላለሁ
አምላኬ/2/ ላክብርህ ልነሳ
ልውደቅ ተንበርክኬ
አንተማ ፍቅርህን ስትሰጠኝ
አንተማ ከቶ አልቆጠብክብኝም
አንተማ በምህረትህ ብዛት
አንተማ አጠገብካት
አንደበቴ ፅድቅህን ተናግሮ
አይጨርሰው አንዱንም ዘርዝሮ
ለደከመው ጉልበት ብርታት ሆንህ
በዓለም ከብረህ አምረህ ደምቀህ ታየህ
አንተማ የፅድቅ አምላክ ጌታ
አንተማ ሁሉን የምትረታ
አንተማ በጭንቀቴ ሰዓት
አንተማ መድህን ሆንከኝ ብርታት
እኔማ እንዳልርቅ ከደጅህ
እኔማ እንዲያነፃኝ ደምህ
እኔማ ከልብህ ጎዳና
እኔማ በማስተዋል ልፅና
በምህረትህ በፍቅርህ ነው
ለበጎችህ የምትሰራው
ፍቅርህንም ያየሁ ጊዜ
ብዬ ጠራሁ ኢየሱሴ
