ታምራቱን እየጨመረ
ይገርመኛል እያደረ
ታዲያ እግዚአብሔር እኔን ወዶ
አይኔ አያይም ከሱ ማዶ /2/
ስጠራው ድምጼን ይሰማል
ታምራት በጁ ይሆናል
ይመጣል ብዬ በጊዜው
አፍሬ አላውቅም ታምኜው /3/
ታምኜው /2/ አላውቅም ባክኜ
ትርፌ ነው ያየለው ማምለኬን የጨመረው
ትከሻው ሰፊ መስሎ ተማምኖ
ከዳር ሳያደርስ ከመኃል ጥሎ /2/
አይሄድም ጌታ ከተሸከመ
እንደኔ ይመስክር የተገረመ
መዝሙር ነው ቃሌ ሁሌም በቤቱ
ለኔ ካበዛው ከታምራቱ /2/
ዛሬም መች ተወኝ የለውጥ አባቴ
ያዘምረኛል ይኸው በህይወቴ
