በኃይሉ አይበረታም ባንተ ካልታገዘ
ትርፉ ኪሳራ ነው ሰው አንተን ካልያዘ
ቀኝህን ተማምኖ እርሱ ግን ያረፈ
ማሸነፍ ይችላል ከቃልም ባለፈ
አንተ መፍትሔ አለህ /2/
ጌታ ሁሉን ቻይ ነህ
ከእሳት ታወጣለህ
ከአፈር ታነሳለህ
ከሞት ታድናለህ
የድል ጎዳና ነው የአንተ እርምጃ
ሀሳብህ አይነጥፍ በሰዎች ደረጃ
ከፊት እየወጣህ በፍቅር ስትመራ
ማሸነፍ ይቻላል ጌታ ካንተ ጋራ
ጌታ ካንተ ጋራ
የለም የሚያስፈራ
ኣንተ ስትሰራ /2/
ማሸነፍ ካንተ ጋራ
ይቻላል ሰው ከፀና
እግዚአብሔር ትችላለህ
ላመነህ መፍትሔ አለህ /2/
