የታመንኩበት የተደገፍኩበት
ሰርቶ ጌታ ይኸው አየሁት
ታመኑት ዛሬም ተመኩበት
ድንቅ ነው ጌታ በእውነት ለጠበቁት /2/
ምንም ቃላት አይወጣኝም ከአፌ
ዝምታ ነው በቃ የኔ መልሴ
የቱ ቃል ነው አንተን የሚገልፅህ
በሕይወቴ በዛ ታመራትህ
ማን ልበልህ ምን ልበልህ
ላንተ ቃላት አጣሁልህ /2/
1. አስገረምከኝ አስደነከኝ በኑሮዬ
ሰማህልኝ መለሰክልኝ ልመናዬን
ያረክልኝን ውለታ እቆጥራለው
ድንቅ ስራህን እያየሁ እገረማለው /2/
ማን ልበልህ ምን ልበልህ
ላንተ ቃላት አጣሁልህ /2/
2. በምን ቃላት በምን ቋንቋ ይገለፃል
ስራህ ግሩም ከአይምሮ ሁሉ ያልፋል
ብመራመር ባስበው አልደርስበት
የደግነት የፍቅርህን ስፋት ጥልቀት /2/
የታመንኩበት የተደገፍኩበት
ሰርቶ ጌታ ይኸው አየሁት
ታመኑት ዛሬም ተመኩበት
ድንቅ ነው ጌታ በእውነት ለጠበቁት /2/
3. አይቀመጥ አይቋጭም ደግነትህ
በሕይወቴ ያበዛኸው ታምራትህ
ያየኝ ሁሉ ምስክር ነው በእኔነቴ
ስትረዳኝ ስታግዝኝ በሕይወቴ /2/
ምንም ቃላት አይወጣኝም ከአፌ
ዝምታ ነው በቃ የኔ መልሴ
የቱ ቃል ነው አንተን የሚገልፅህ
በሕይወቴ በዛ ታመራትህ /2/
ማን ልበልህ ምን ልበልህ
ላንተ ቃላት አጣሁልህ /2/
አግዞኛልና ጌታ አግዞኛልና /2/
እረድቶኛልና ኢየሱስ እረድቶኛልና /2/ /2/
ጠብቆኛልና ጌታ ጠብቆኛልና /2/
