ኦ እጅግ ክብር ቁርባን
እግዜር የሚመግበን
አምናለሁ ደግሞም እርሱን
እርሱም ተናግሯል ይሁን
ሲያስተምር ለካህናት
እንደኔ አድርጉ በእውነት
የኔ ስጋ ነው ብሉት
ደግሞም ደሜ ነው ጠጡት
ሳይተው ሰማይንም
በመንበር ላይ ይኖራል
ከዚሁም ይቀመጣል
ደስታችንም ይሆናል
በቅዳሴ ጊዜያት
ይቀደሳል በእርሱ ስም
ያን ጊዜና ሰርክለት
ይታዘዛል ለቄስም
የእንጀራው ህላዊ
መልኩ ብቻ ሲቀር
ደግሞም የወይኑ ህላዊ
ተለውጧል በሚስጥር
ይህን ሚስጥር እንመን
እናመስግነው እርሱን
አይናችን ቢሳሳትም
ያስረዳል ሐይማኖት
