ሁሉም ለመልካም ነው

256

ሁሉም ለመልካም ነው ሁሉ ለበጎ ነው /2/
አንተ አትሳሳትም እኔ አምንሀለሁ
አንተ ትክክል ነህ እኔ አውቅሀለሁ
አሁንም አንተው ነህ የኔ ተስፋ /4/

ስጋዬ ቢቆስል መንፈሴ ቢጎዳ
አለኝ ብዬ ያልኩት ሳልስበው ባጣ
ለምን አልልህም እግዚአብሔር ጻድቅ ነህ
በምትሰራው ስራ ሁሌም ትክክል ነህ /2/
አሁንም አንተው ነህ …

ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ ነህ አውቅሀለሁ
አንተኑ ታምኜ እጠብቅሀለሁ
አንተ ያስብክልኝ መልካም ነው ይሻላል
አይወዳደርም ከሁሉም ይበልጣል /2/
ሁሉ ለመልካም ነው……..

አትቸኩልም ጌታ ደግሞም አትዘገይም
ቀስ ብለህ ብትሄድ ማንም አይቀድምህም
ነገርን በጊዜው ውብም ታደርጋለህ
ታሪክን ቀይረህ ታምር ትሰራለህ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top