ሁሉንም አየሁት
መረመርኩት ፈተሽኩት
ጌታዬ ልዩ ነው ፈቅጄ አመለኰት /2/
ተራራ ላይ ወጣሁ ምድርን አሰስኩኝ
እንደጌታ ያለ ማንም አልገጠመኝ
መመካት ባንተ እንጂ መታመንስ ባንተ
በሰው መደገፍስ አይኖር እንዳሽተ
ወደር አጣሁልህ ለክብርሀ መግለጫ
ቦታም አላገኘው ለአንተ መቀመጫ
አምላክ አልተገኘ ለአንተ መለወጫ
ይህው ስመካብህ ኢየሱስ የእኔ ምርጫ
ነፍሴ እፎይ አለች ተረጋግታ አሁን
ኢየሱስን ይዛለች መድህን የሆነውን
ተባረክ ተባረክ ተባረክ እላለሁ
ለእኔ መደረጉን ለሁሉ እነግራለሁ
ተወደስም ብዬ መቼ እኔ እጠግብና
ኢየሱሴ ልዩ ነህ የሆንክ ባለዝና
ላመስግንህ በልቤ በነፍሴ ዙፋን
አቻ ስለሌለህ ልበል ተመስገን
