ሰዎችም ተላኩ ወደታዘዘበት
ፈተውም ሊያመጡ ከታሠረችበት
ታላቅ ምስጢር ያላት ሰው ያልተቀመጠባት
እንዲህ ያዘጋጃል ጌታ ሊከበርባት
ሆሳዕና ስሙ የተባረከ ነው በማለት
ዘንባባችንን አንስተን እልል እንበል
የታጨች ውርንጭ ለበሰች አጌጠች
የጽዮን ጌታ አስቀምጣ ተጓዘቸች
ምንስ እንላለን ዝቅ ያለው ተመርጧል
የዓለም መድኃኒትን ሊይዝ ይሸለማል
ተንቃ ተጥላ ተዋርዳ እንዳልነበር
አምላክ ከመረጣት በእርሷ ለመክበር
ማነው የሚሟገት የሚከራከር
አትገባም ብሎ ደፍሮ የሚቆም
እንዴት ዝም ያሰኛል ድንቅ እየተሰራ
ስለንጉሣችን እስከዳር ይወራ
ሕዝቦች እልል በሉ በፊቱም ስገዱ
ዘንባባና ልብስን ለክበሩ እንጥፉ
የከበር ከብራል እየሱስ እዩ
ክብር ላንጉሥ ሆሳዕና በሉ
የከበር ከብሯል እየሱስ እዩ
ክብር ለንጉሡ ሆሳዕና በሉ
