ሆሳእና

282

ሆሳእና/4/
ሆሳእና ምስጋና /8/

ክቡር መኳንንቶች በሮችን ክፈቱ
ለመሲሁ ክብር ሆሳእና በሉ
ተከብሮና ገኖ በሰልፍ የሚያልፈው
ክርስቶስ ኢየሱስ በእውነት ጌታችን ነው

እየሩሳሌም ሆይ ዘምሪ በደስታ
ለንጉሱ ክብር ከበሮ ይመታ
ሰዎች ዝም ብንል ግኡዝ ይናገራል
ከሊቅ እስከ ደቂቅ በሆታ ይዘምራል

ዘንባባን እንዘንጥፍ እንዘምር በእልልታ
ለንጉሱ ክብር ላረገው ውለታ
ሊገረፍ ሊስቀል ይህን እያወቀ
በውርንጫ ጀርባ ለፍቅሩ ወደቀ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top