1. ሰላም /2/ ብዬ ልጀምር ምስጋና
ለአዛኝቷ ማርያም ይገባታልና
እንደብሩህ ኮከብ የሚያበራው ፊቷ
የምህረት እናት ጌታን ወላዲቷ
ለማርያም እናቴ ምስጋና አቀርባለሁ
የሷን ስም ጠርቼ ስርየት አገኛለሁ /2/
2. የአዳም ልጆች ሐጥያት ፍፁም ያልነካሽ
ቅድስት ድንግል ማርያም ብፅእት የሆንሽ
ለክብርሽ ልዘምር ለድንግልናሽ
አማላጅዋ ማርያም ምስጋና ይግባሽ
ለማርያም እናቴ ምስጋና አቀርባለሁ
የሷን ስም ጠርቼ ስርየት አገኛለሁ /2/
3. ሰላም ማርያም ብዬ ስምሽን እጠራለሁ
ገድልሽን በሰው ፊት እመሰክራሁ
ዘወትር ለስምሽ በአፌ ዘምራለሁ
ጧት ማታ ከልቤ አመሰግናለሁ
ለማርያም እናቴ ምስጋና አቀርባለሁ
የሷን ስም ጠርቼ ስርየት አገኛለሁ /2/
