ለዘላለዓለም ትኖራለህ

227

አንተ ግን አንተ ነህ /3/
ለዘለኣለም ትኖራለህ ህያው ሆነህ /2/
አንተ ግን ያው አንተው ነህ /3/
ለዘላአለም ትሮራለህ ሃያው ሆነህ /2/

በዘመናት ሁሉ አንተ ትፈራለህ /2/
እግዚአብሔር ትልቅ ትልቅ ነህ /2/

ምድር ትናወጣለች በሀይልህ ትነዳለች
ተራሮች ይጠፋሉ ክብርህን ሲያዩ ይቀልጣሉ
አንተ ግን ለዘላለም ሚስተካከልህ የለም /2/
ተፈርተህ በመንግስትህ ሕያው ሆነህ ትኖራለህ /2/

ነገሥታቶች ሲነሱ ምድርን ሲያናውጡ
በሐይል በጉልበታቸው በድፍረት ቢገለጡ
አንተ ግን ከሀይላቸው ከጉልበታችው በላይ ነህ /2/
መንግስትህ ሳይደፈር እንደነገስክ ትኖራለህ /2/

አመታት የማልቅብህ የሚጋፋህ የሌለህ
የምትኖር ለዘላለም እንዳንተ ለ ማንም የለም
ለዘመናት የተመለክ ዛሬም አዲስ ጥንት የነበርክ /2/

ከአንተ በላይ ማንም የለ የሁሉ ራስ መሰረት ነህ /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top