ሊቀ ካህኔ

286

ከናቴ ማህፀን ሳለሁ ገና አሰብከኝ
እኔ መች ገባኝ ለክህነት ስትመርጠኝ .
በጎቼን ሰብስብ አግድ ስትለኝ
እረኛ እንድሆን ስልጣን ስትሰጠኝ

አንተ ሊቀካህን
አንተ የኔ ነብይ /2/ እግ/ር አንተ እንዲህ መከርከኝ

የሰጠሁህን ስልጣን ተጠቀመው አልከኝ
በውስጤ ያለውን ቃልህን እንድሰብከው
የወንጌሉንም እውነት እንድገልጠው

ሊቀካህኔ እየሱሴ የሆንከኝ ጠበቃዬ
እኔን ልጅህን መረጥከኝ ካህንም አደረግከኝ

እግ/ር አልከኝ ቃልህን ተናገርከኝ
ማይደመሰስ ማህተም መታህብኝ
እንደመልከ ጼዲቅ ሹመትን ሰጠኸኝ
ለዘለአለም ካህን አደረከኝ
አንተ ሊቀካህን……..
ሊቀካህኔ እየሱሴ……..

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top