ናናና መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና
ናናና መንፈስ ቅዱስ ሆይ ና
ይኸው ተሰባስበን እንጠብቅሃለን
ናና ተቀጣጠል ዛሬም በመሃላችን
ነበልባል እሳትህ የሚማርክ ፍቅርህ
ዛሬም ይፍሰስልን ቅዱስ ሥራህ
ልባችንን ከፍተን እንጠራሃለን
በየስጦታችን ሥራህን አሳየን
ና መንፈስ ቅዱስ ሆን አንድድ አሳትህን
ቀድስ ልባችንን ስፈን በመሃላችን
ውብ አንደበታችን የኛ ጠበቃችን
ሊረታን የመጣ ይፈር ጠላታችን
ክፉውንና ደጉን እንድናውቅ ለይተን
ሙላን ጥበብህን እናውራ ሥራህን
ያዘነውን አፅናኝ ሰባራውን ጠጋኝ
ጨለማን ገፋፊ እውነተኛ ብርሃን
ና መንፈስ ቅዱስ ሆይ ሙላን ልባችንን
ዛሬም እንደጥንቱ አብብ በውስጣችን
