1. ምህረት እውነት ስለበዛ
በማለዳ ምህረትን ስለጠገብን
እናመሰግንሃለን /2/
ሁልጊዜ ምስጋናህን እናበዛለን
ምስጋናህን እናበዛለን /4/
ታምራትህን እናወራለን /4/
ምህረትህን እንዘምራለን /4/
ክብርህንም እናየዋለን /4/
2. ዕለት ዕለት ማዳንህን
ዝናህንም ለአህዛብ እናወራለን
እናመሰግንሃለን /2/
ሁልጊዜ ታምራትን እንመሰክራለን
ምስጋናህን እናበዛለን /4/
ታምራትህን እናወራለን /4/
ምህረትህን እንዘምራለን /4/
ክብርህንም እናየዋለን /4/
3. እንጨት ውሃ በሌለበት
በምድረ በዳ ነፍሴ አንተን ናፈቀችህ
እኔ ተስፋ አደርግሀለው /2/
ሁልጊዜ ወደ አንተ እገሰግሳለሁ
ምስጋናህን እናበዛለን /4/
ታምራትህን እናወራለን /4/
ምህረትህን እንዘምራለን /4/
ክብርህንም እናየዋለን /4/
4. መአት ቁጣህ እራቀልን
በቸርነትህ ወደቤትህ መግባት ቻልን
እናመሰግንሃለን/2/
ሁልጊዜ ምህረትህን እንዘምራለን
ምስጋናህን እናበዛለን /4/
ታምራትህን እናወራለን /4/
ምህረትህን እንዘምራለን /4/
ክብርህንም እናየዋለን /4/
5. በፅድቅህ ፊትህን እናየዋለን
ክብርህንም ስናይ ጌታ እንጠግባለን
እናመሰግንሃለን/2/
ሁልጊዜ የአንተን ክብር እናወራለን
ምስጋናህን እናበዛለን /4/
ታምራትህን እናወራለን /4/
ምህረትህን እንዘምራለን /4/
ክብርህንም እናየዋለን /4/
