ምስጋና እናቅርብ

65

ለኛ ያለው ፍቅር ቢገፋፋው ጌታ
አርባ ቀን ከሌት እጅግ ተንገላታ
ይህ ሁሉ ስቃይ ይህ ሁሉ ፍዳ
ሊከፈልልን ወዶ ነው የኛን እዳ

ግንድ ላይ ታስሮ የሾህ አክሊል ደፍቶ
በሐሩር በውርጭ ያ ውበቶ ጠፍቶ

ይህ ሁሉ ስቃይ ይህ ሁሉ ፍዳ
ሊከፍልልን ወዶ ነው የኛን እዳ

ምስጋና እናቅርብ ለጌታችን
በምድር ላይ መጥቶ ያዳነን እርሱ ነው
ምስጋና እናቅርብ መድሐኒታችን ነው

የኛን ጭንቅ አይቶ ሊያወጣን ከመከራ
ስድብ ግርፊያውን ሁሉ ችሎ በተራ
ይህ ሁሉ ስቃይ ይህ ሁሉ ፍዳ
ሊከፍልልን ወዶ ነው የኛን እዳ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top