እመቤታችን በክብር ተቀምጣለችና
ለአሕዛብ ምህረትን ለምናለችና
ለመንግስተ ሰማይ በር ሆናለችና
ለክርስትያኖች ሁሉ ታስገባለችና
ጻድቃኖች በሰማያት በአንድነት ይኖራሉ
ጣፋጭ መዝሙራቸውን በዓለም ላይ ይዘምራሉ
እስከዘለአለም በደስታ ዘወትር ይኖራሉ
ሁልጊዜ ምህረቷንና ክብሯንም ያወራሉ
ሰላማዊ የሰላም እናት ለአለም
ፍቅራችንን ጠብቂ ለዘለአለም
ሰላማዊት የሰላም እናት ለአለም
የክርስቶስ እናት ኮከብ ለአለም
የፃድቃኖች ኮከብ ማርያም ናት /2/
ለተሰቀለው እየሱስ ክርስቶስ እናት ናት
ለክርስትያኖች ሁሉ እናት ሕይወት ናት
ጽጌረዳ አበባ መዓዛችን ናት
ልመናዋም በሰው ዘንድ ቅዱስ ሆኖ ይኖራል
ብርሐኗም ለአለም ለዘላለም ያበራል
ምሕረቷ በአለም ሁልጊዜ ይኖራል
ሃይልና ብርታትንም ዕለት ዕለት ይጨምራል
