1. እንብላ አብረን ቀርበን
ስጋ የህብረትን
እግዚያብሔር ይሰብስበን
አንድነት እንድንሆን
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
2. አምላክ ያዘጋጀው ምግብ
ለመብላት ኑ እንቅረብ
ክርስቲያኖች ነንና አንድ
ምንም አይለየን በግድ
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
3. ከዚህ ገበታ እንቅረብ
ይዘን የታጠበ ልብ
እንዲደሰት እንዲረካ
በጌታችን ፋሲካ
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
4. ሃጢያተኛም በምህረቱ
እንዲቀርብ ከታቦቱ
ደሃና ሐብታም ሳይል
ጋብዞናል ለመብል
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
5. ካባቱ ጋር እንደሚኖር
እንዳንለይ ከርሱ ጋር
መንፈስህን ላክልን
ሊመራን ሊያፋቅረን
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
6. ስንሳተፍ ከመስዋዕት
ያሰቀለውን በእንጨት
ይቅርብን ቂምና በቀል
ወንድምን የሚበድል
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
7. ዛሬ አብረን እንሁን
ለመካፈል ህብስቱን
እንድንሳተፍ ክብሩን
አብሮ ነው የጠራን
ስጋህን ስንካፈል
አንዳችን እንቢ ሳንል
በወንድሞቻችን ፍቅር
ከአምላክ ጋር እንተሳሰር
