- በመንበርህ ቤተክርስቲያን
ከፍተህልን የህይወት መግቢያን
የደከመው ባንተ አርፏል
ገበታህም ፅዋው ተርፏል
ያለ እየሱስ ለምትደክሙ
ላቆሰለው ሀጥያት ሸክሙ
እንኩ ያለን ሳይገባን
መድሀኒት ነው ቅዱስ ቁርባን
አዝ:- እየሱስ እራሱን ሰጠን
በኛ ውስጥ ሊኖር መረጠን
ሲያከብረን ሲያሳየን ፍቅሩን
ሰቶናል ቁርባነ ሚስጥሩን
እየሱስ በቅዱስ ቁርባን
በኛ ውስጥ ሊኖር ተገባን
ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን
መንግስቱ ዳግም አገባን
ኢየሱስ ህይወትን ሰጠን /3/
ለመንግስቱ ዳግም አገባን
- ስጋውን ለኛ የቆረሰ
ክቡር ደሙ ነው የፈሰሰ
ለስጋም ለነብስም መድህን
እንቅረብ በፍርሀት አሁን /2/
አዝ:- እየሱስ እራሱን ሰጠን
በኛ ውስጥ ሊኖር መረጠን
ሲያከብረን ሲያሳየን ፍቅሩን
ሰቶናል ቁርባነ ሚስጥሩን
እየሱስ በቅዱስ ቁርባን
በኛ ውስጥ ሊኖር ተገባን
ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን
መንግስቱ ዳግም አገባን
ኢየሱስ ህይወትን ሰጠን /3/
ለመንግስቱ ዳግም አገባን
- ክቡር ደሙን ለኛ አፍስሶ
ከአካሉ ስጋውን ቆርሶ
ታላቅ ሚስጥር አካፈለን
የዘላለም ህይወት ሲለን
መንገዱ ነው የመዳኑ
አሜን ብለው ለታመኑ
በንስሀ መንገድ ፅኑ
ወደ ሚስጥረ ቁርባን ኑ
አዝ:- እየሱስ እራሱን ሰጠን
በኛ ውስጥ ሊኖር መረጠን
ሲያከብረን ሲያሳየን ፍቅሩን
ሰቶናል ቁርባነ ሚስጥሩን
እየሱስ በቅዱስ ቁርባን
በኛ ውስጥ ሊኖር ተገባን
ክርስቶስ በቅዱስ ቁርባን
መንግስቱ ዳግም አገባን
ኢየሱስ ህይወትን ሰጠን /3/
ለመንግስቱ ዳግም አገባን
