ቅዱስ ቅዱስ

146

ቅዱስ /3/ አሸናፊ እግዚአብሔር
በስማይ የሚኖር እንዲሁም በምድር
ይገበዋል ለእርሱ ምስጋናና ክብር

በረቂቅ ጥበቡ ጥበብን የዘራ
ምድርን በባሕር ላይ በቃሉ ያፀና
መሃሪ ይቅር ባይ ቸር አምላክ ነውና
እጃችሁን አንሱ ለስሙ ምሥጋና

ቀድሞ የነበረው ዓለም ሣይፈጠር
ሁሉን አሳልፎ ዘላለም የሚኖር
ክብሩ ጌትነቱ ሥልጣኑ የማይሻር
አልፋና ኦሜጋ ፈጣሪያችን ይክበር

በመልኩ በአምሣሉ እኛን የፈጠረ
ብንገኝም እንኳን በደለኞች ሆነን
በልጁ በኢየሱስ ከውድቀት አንሳን
ቅዱስ ቅዱስ እያልን ስሙን እንጠራለን

ቀኑ ቢመሽና ሌሊቱ ቢጨልም
ጌታ ከኛ ጋር ነው የሚያስፈራን የለም
ቀኑ ቢመሽና ሌሊቱ ሲጨልም
ጌታ ከኛ ጋር ነው የሚያስፈራን የለም

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top