ቅዱስ ነው ጻድቅ ነው ጌታ በስራው
አንዳች አልተገኘም ከቶ የሚሳነው
አድርጓል አይተናል ድንቅ ታምራቱን
ለለመኑት ሲሰጥ ሲያሳይ በጎነቱን
ድቅን ብሉበት ባህር ፊት ለፊቱ
ሙሴ ግራ ገባው ደርሶበት ጠላቱ
በትሩን አንስቶ በእምነት ሲመታ
ድንገት ተከፈለ ባህሩ ሁለት ቦታ
ጠላት አልጎዳውም አልደርሰበትም
ራሱ ሰጥሞ ቀረ ባህሩ ሲገጥም
ሀና መች አፈረች ጌታዋን ጠይቃ
እንባዋ መጉረፉ ፍጹም አንዲያበቃ
ጊዜውን ጠብቆ ሳሙኤልን ሲሰጣት
የለቅሶ ህይወቷ እዛ ላይ አበቃለት
ሀናንም ጸሎትን አልከለከላትም
ስትለምን በቤቱ አላሳፈራትም
ልጅቷ ሞታለች አታድክም መምህሩን
ብሎ ሰው ሁሉ ሲያስተው ልመናውን
እመን እንጂ አትፍራ ትድናለች ብሎ
ከቤቱ ገባና ተነሽ አላት ቶሎ
ከሞትም አስነሳት ሰው ሁሉ እያያት
ማመን አቃታቸው ነፍስ ሲዘራባት
