በቃ ወስኛለሁ

165

በቃ ወስኛለሁ አልወጣም ከፍቅርህ
ተመቻችቻለሁ አምሮብኝ በቤትህ
አንተ ሆነሃል መድህኔ /2/
ለእኔ የዘላለም /2/

ገና ጨቅላ ሳለሁ አፌ ሳይፈታ /2/
አውቄ አደኩኝ ፍቅርህን የኔ ጌታ /2/
ምንም ነገር የለም ከአንተ የሚለየኝ /2/
አንዳንተ ትከሻ የለም የተመቸኝ /2/

እጅህን የለመደ መች ሌላ ይመኛል /2/
አንተን ከሌላ ጋር መች ያወዳድራል /2/
አንድና አንድ ነው ኣንተው ነህ መመኪያው /2/
እኔ ምስክር ነኝ በእጅህ ስለበላው /2/

ፍቅርህ ማርኮኛል ሌላ እንዳልመኝ /2/
ምርጫ ቢበዛልኝ እኔን አይለውጠኝ /2/
በአንተ ተማርኬ እጄን እሰጣለሁ /2/
የዘለአለሜ ነህ በቃ ወስኛለሁ /2/

የሆሳዕና

Leave a Comment

Scroll to Top