በእግዚአብሔር እንመን

73

የፍቅር ጐዳና ነው የሰላምም አምላክ
በእግዚርአብሔር እንመን ልባችን አይታወክ /2/

የደረቀውን ልብ አውጥቶልን ከኛ
የሸሸውን እምነት መልሶ ወደኛ
እረፍትን ሰጥቶ ለተናወጠ አእምሮ
ሁሉንም ይለውጥ ሰላምን ጨምሮ

በምንሄድበት ለሰላም ከሄድን
በምንጠራበት ለበጐ ከተጠራን
በወንድሞች መሐል በፍቅር ከተጓዝን
ይበዛል ለኛ የፀጋው መጠን

እንግዲህ በእምነት ጸንተን ከፀደቅን
በጌታ በኢየሱስ ይዘን ሰላምን
የፍጡር አዳኝ ነው ተከላካይ ሐይላችን
ስለሁሉም ሰላም ያፍስ በልባችን

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top