በደለኛ ነኝ

245

በደለኛ ነኝ ጌታ ሆይ ኃጢያተኛ
ምህረትን እጠብቃለው ጌታ ፈጥነህ ድረስልኝ /2/

ጠፍቼ ነበረ በዚህ ክፉ አንደበቴ
ይቅር እንድትለኝ መጣሁኝ አባቴ
ከባከነው ላይ ፊቴን አዙሪያለው
ምህረትህን እተማመናለው

የስራሁት ኃጢያት እስከመቼ ይግዛኝ
ድካሜ በርትቶ አንገቴን ሲያስደፋኝ
ምህረትህ በዛልኝ ድካሜም አለፈና
ፍቅርህን ላውራ ልመስክር እንደገና

በሀሜት በማግለል ሰው ሁሉ ሲጠላኝ
መሄጃ አጥቼ መጣሁ እንድትረዳኝ
ሀሜቱም ቀርቶ ማግለሉም አለፈና
በአንተ ምህረት ሰው ሆንኩኝ እንደገና

ለፋሁኝ ደከምኩኝ ለማይሞላው ኖሮዬ
ቤትህ ይሻለኛል አስገባኝ አባብዬ
ቃልህ በውስጤ እንደእሳት ይቀጣጠል
ላመስግንህ ሁሌ ለአንተ እልል ልበል

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top