ባወራው

235

አዝ ባወራው ባወራው ብናገረው /2/
አያልቅም የሰራልኝ ነገር

አንድ ሁለት እያነሳሳው ብዘምረው
የጌታዬን ብዙ ውለታ ብናገረው
አልጨረስኩም የኽው ዛሬም እንደገና
ተነግሮስ መቼ ያልቅ እረ እኔስ ገና አለ ገና
ባወራው ብዘረዝረው አያልቅም ጌታዬ ሥራው /2/

ደግነቱን አስብና ክበር ስለው
ደግሞ ፍቅሩ ግድ ይለኛል ለእኔ የዋለው
ታዲያ ላዚምለት እንጂ በየተራ
በዚህስ መቼ ያበቃና ተነግሮስ መቼ ያልቅና
ውለታው ቤቴ ሙሉ ነው በዛብኝ ብዘረዝረው /2/

የጌትዬ ፍቅሩ ውለታው ብዙ ነው
በአንደበቴ ተናግሬ ማልጨርሰው
ሳነሳሳ ውዬ ባድር አልሰለችም
ኢየሱስ የጌቶች ጌታ ድንቅ ነው የእርሱ ውለታ
ባወራው ብዘረዝረው ጌታዬ ስራው ግሩም ነው /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top