ብፅእት ናት

199

ብፅእት ናት /3/
እናታችን ማርያም ብፅእት ናት

ተላከ መላኩ ገብርኤል
ማርያም ወደምትባል ድንግል
በቅድሚያ መልእክቱ ሳይጀመር
ሰላምታ አቀረበ እንዲህ ሲል

ደስ ይበልሽ ፀጋ የተሞላሽ
ከሴቶች የተባረክሽ ነሽ
መላእኩ እንኳን እንዲህ ያከበራት
ምንኛ ብፅእት ድንግል ናት

መላኩ ገብርኤል በመቀጠል
መልእከቱን ከነገራት እንዲህ ሲል
በጌታ ሞገስ አግኝተሻል
የሉኡል ሐይል ይፀልልልሻል

እነሆ ወንድ ልጅ ትወልጃለሽ
ስሙንም ኢየሱስ ትይዋለሽ
ጌታ ከአንቺ ሊያድር እጅግ ወዷል
እናቱ እንድትሆኚ መርጦሻል

እግዚ/ር ከእሷ ጋር የሆነ
ኢየሱስ በማህፀኗ ያደረ
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላሽ
የስላሴ መቅደስ የሆንሽ

እነሆ እኔ የጌታ አግልጋይ ነኝ
አንተ እንዳልከው ይሆንልኝ
በማለት ፍቃዷን የሰጠች
የጌታችን እናት ብፅእት ነች

ልጇን ሁሌ የምታሰላስል
የሚላችሁን አድርጉ የምትል
አንድ ላይ ከሐዋሪያቶች ጋር
በፀሎት የምትተባበር
ትውልድ ሁሉ ብፅእት የሚላት
የጌታችን እናት ብፅእት ናት

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top