ተሳስቼ ስጓዝ በማላውቀው መንገድ
ስንከራተት ኖርኩኝ በእውኔ እንደ እብድ /2/
ለካስ ጌታ አለኝ ከእሳት የሚያወጣ
ከተራራ ገደል ካባጣ ጉባጣ
ምንም አላገኘው ተንከራተትኩኝ
ተመለስኩ ጌታ ሆይ እባክህ ተቀበለኝ
መንገዱ ብርሐን ነው የጌታዬ ኢየሱስ
አየሁት ሁሉንም ስዳስስ ስዳብስ
ያለኝ ሐይል ጌታዬ እረዳቴ ነው ለኔ
ባደረኩት ጥፋት አለብኝ ኩነኔ
ጠይቄ አላጣሁም ከእርሱ የምፈልገው
ሰሚ ነው ጌታዬ ስጠኝ እሱ ካለው
አለም አታላይ ናት ለኛ ለግዙፎች
እንከተል ጌታን መንገዱ ማይሰለች
መኖር ሲያስፈልገኝ ህይወቴን አድሼ
እኔ ግን ወደኩኝ ትዛዙን አፍርሼ
በሰራሁት ሐጥያት እርሱ አልጣለኝም
መሐሪ ነውና አልጠራኝም ለዘለአለም
