እንግዳ ነኝ እኔ ስኖር በዚህች አለም
ሃብቴም በሰማይ ነው ከዚህ ምንም የለም
መላዕክት ይጠሩኛል ከሰማይ በር ከፍተው
ከእንግዲህ ይህ አለም ፍፁም ቤቴ አይደለም
ታማኝ ወዳጅ እንዳንተ እንደሌለኝ
ጌታ ሆይ ታውቃለህ እኔን የሚያፅናናኝ
መላዕክት ይጠሩኛል ከሰማይ በር ከፍተው
ከእንግዲህ ይህ አለም ፍፁም ቤቴ አይደለም
ወደፊት ልራመድ ይጠባበቀኛል
የሱስ ይቅር ብሎ በሩን ከፍቶልኛል
ምንም ደሃ ብሆን እኔን አይተወኝም
ከእንግዲህ ይህ አለም ፍፁም ቤቴ አይደለም
አፍቃሪ አዳኝ አለኝ በላይኛው አለም
ናፍቆቴን አልተውም ፊቱን እስካይ ድረስ
በሰማይ ደጅ ቆሞ ይጠባበቀኛል
ከእንግዲህ ይህ አለም ፍፁም ቤቴ አይደለም
በላይኛው ሃገር በአንድ እንኖራለን
ከቅዱሳን ጋራ በድል እልል እያልን
የተወጋውን በግ በዓይናችን እያየን
ባልተሰማ ዜማ ክብሩን እንገልፃለን
