ምስጋና ይሁን ለጌታ ኢየሱስ
ክብር ይሁን ለኛ መድሐኒት
ደሙን ያፈሰሰው ሰለሁሉም
ከፍ ከፍ ይበል ቸሩ መድሐኒያለም
ክብር ዙፋኑን ወደ ጐን ጥሎ
ከአለም መጣ ስለኛ ብሎ
ከንፅእት ድንግል ማርያም ተወልዶ
ፍፁም ሰው ሆነ እራሱን አዋርዶ
በእጅ በእግሩ ላይ በሚስማር ተወግቶ
ስለ ሰዎች በመስቀል ሞቶ
ሕይወትን የሚሰጥ እንዲያው በነፃ
መድኃኒያለም ነው ከሐጥያት የሚያነፃ
ሰውን የሚያድን የሱስ ብቻ ነው
ከእግዚያብሔር ለኛ የተሰጠው
ከተከተልነው መድሐኒያለምን
መንግስተ ሰማይን እንወርሳለን
ስለዚህ የእግዚያብሔር ተከታዮች
ጌታን የምታምኑ ክርስትያኖች
እዳችሁንም እንደከፈለ
እወቁ ለእናንተ እንደቆሰለ
