ነጋልቃ እኔስ ነጋልኝ
ዳግመኛ ላይጨልምብኝ
ከሰማይ ሰማያት ወርዶ
አሳየኝ እውነትን ገልጦ
ኢየሱስ/3/ የነፍሴ ንጉስ
ኢየሱስ/3/ የሰላም ንጉስ
በትንቢት ሲነገር ለብዙ ዘመናት
አለምን የሚያድን ከጨለማው ግዛት
ትንቢቱ ሰመረ ለወጠው ህይወቴን
እውነቱ በራልኝ አውጅኩ ነፃነቴን
ከሰማይ ሰማያት ክብሩን ሁሉ ትቶ
በረት ተወለደ እራሱን አዋርዶ
በሃጥያተኛው ልቤ ኢየሱስ ነገሰ
ነፍሴም እፎይ አለች ሰላሙ ፈሰሰ
የቱ ስራዬ ነው እንዲህ ያስወደደኝ
ራሴን ስመለከት አንድም ነገር የለኝ
በፀጋው ነው እንጂ እንዲያው በምህረቱ
ክብሩን ያስተወው የፍቅሩ ብርታቱ
