አለኝ ብዙ ምስጋና

100

አለኝ ብዙ ምሥጋና ላንተ ሚሰዋ ገና
ምስጉን ነህ አንተ ሁሌ መልካም ስመገናና
ልበል እንጂ አንተ መልካም
ውለታህን እኔ አልረሳም
ላመስግንህ የእኔ ጌታ
ሳልሰላች ጠዋት ማታ

ገና ሳላውቅህ አወከኝ ለራስህ
መርጠህ ቀባኸኝ
የልጅነት ሥልጣን ሰጥተህ
የመንግስትህ ወራሽ አረከኝ
አገዛዝህ ምቹ ነው አልሄድ እኔስ ወደሌላ
ግዛኝ አንተ ለዘለአም ሁንልኝ የኔ ከለላ

ያዘኝ አትልቀቀኝ እስከ መጨረሻ
ሌላ እኔ የለኝም ከክፉ መሸሻ
ላትተወኝ ላትረሳኝ ቃል የገባህልኝ
አስበኝ አባቴ ከቶ እንዳትረሳኝ

ነህ አንተ የዘላለሜ
ዕጣዬ ዕድል ፈንታዬ
ሆኛለሁ እኔ ዕድለኛ
ስለሆንኩ ያንተ ጥገኛ

ለውለታህ መላሽ ሚሆን አጣሁኝ
ፍጽም የሚመጥን
የቃላት መዓት ደርድሬ ልዘምር ምሥጋናህን
ከአእምሮዬ በላይ ነው አምላኬ መልካምነትህ
ፈጽሞ ቃላት አይገልጸው ላንተ ከቶ አይበቃህም

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top