አልረሳውም ጌታ

9

ጐልጐታ ስትወጣ ያደረጉብህን
መስቀል አሸክመው የዘበቱብህን
የሾህ አክሊል ደፍተው ያላገጡብህን
አረሳውም ጌታ ያ የደም ላብህን

ስለኔ ብለህ ነው ጌታ የታረድከው
ልክ እንደወንበዴ በእንጨት ላይ የሞትከው
አንተን ያሰቀለህ የሰዎች ፍቅር ነው
ደምህን ያፈሰስከው ስለበደሌ ነው

አልረሳውም ጌታ ያንን ሁሉ መከራ
ያደረክልኝን በዚያች በጣር ስፍራ

አልረሳውም ጌታ ያንን ጥማትህን
ሰፈነግ የሞላ ኮምጣጤ የሰጡህን
ከቶ አልዘነጋም ያን ቅዱስ ጐንህን
ሲወጉት ደምና ውሃ የወጣውን

ይህንን ሁሉ ጭንቀት ዘወትር አስታውሰኝ
በስቃይህ ኢየሱስ ህይወትን አንዳኝ
በጌተ ሰማኒ ፀሎትን አስተምረኝ
ስትመለስ ጌታ ተኝቼ እንዳልገኝ

የልደት

Leave a Comment

Scroll to Top