አማልጅን

197

አማልጅን/3/ ድንግል

ብፅእት ነሽና ቃሉን በመቀበል
ጌታ ይሰጥሻል አንቺ ከለመንሽ
ኤልሻዳይ ነውና ሁሉን ቻይ ልጅሽ

ማርያም ሁኚ ተገን ለኛ ለልጆችሽ
ከጌታ አስታርቂን ለምኚ ወደ ልጅሽ
አማላጅ ነሽና አንቺን ለለመነ
ወደአምላክ የሄደ ህይወቱን አዳነ

የገብርኤል ብስራት አበሰረሽ አንቺን
ምን አይነት ታዛዥ ነሽ አንቺ እናታችን
ከሁሉ መርጦሻል ጌታ አምላካችን
ሁኝልን ለኛም ተገን አሌንታችን

ጌታን ወለድሽልን ከሐጥያተ ሊያድነን
በመስቀል ላይ ሞቶ ህይወቱን የሰጠን
እናመስግን አንቺን ዳግም ሂዋናችን
ጥበቃሽ አይለየን እመቤታችን

ተመስገኝ ተመስገኝ ሁል ጊዜ ተመስገኝ
አንቺን ለማመስገን ቃላትም አናገኝ
ከተጨነቁት ጋር አብሮ መጨነቅሽ
ምን ፍቅር ቢሆን ነው እንዲህ ያሰገደደሽ

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top