አቁመኝ ባላማዬ

-

አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ያለነቀፋ እንዳገለግልህ
ፀጋህን አብዛልኝ /2/

1. የአንተ አላማ በእኔ
ይከናወን ዘንድ በመፍቀድህ
ከአለም ጠራኸኝ መረጥከኝ
ለወጥከኝ አቆምክኝ በቤትህ
እኔም በመሰጠት ለክብርህ
ለማገልገል አንተን በትጋት
ዓላማዬ ይህ ነው ጌታዬ
ፀጋህን አብዛልኝ እለት እለት

አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ያለነቀፋ እንዳገለግልህ
ፀጋህን አብዛልኝ

2. ዓላማዬ አንተ ነህ እግ/ር
መኖር ለክብርህ በዘመኔ
አንተን ማገልገል ነው መሻቴ
ስለዚህ አትለይ ከጐኔ
የአንተን ተግባር ይግለፅ ተግባሬ
አሳቤ አንደበቴ ህይወቴ
በአላማዬ አቁመኝ ሁልጊዜ
ፀጋህን አብዛልኝ አባቴ

አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ያለነቀፋ እንዳገለግልህ
ፀጋህን አብዛልኝ

3. በዚህ በመጨረሻው ዘመን
ሰው አምላኩን በዘነጋበት
ያንተን ስራ ሰርቼ ልለፍ
ቁም ነገርን ሳለሁ በህይወት
ቅድስናህ ይታይ በህይወቴ
በሃሳቤ በተግባሬ በአንደበቴ
ዓላማዬ ይህ ነው ጌታዬ
ፀጋህን አብዛልኝ አባቴ

አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ባላማዬ አቁመኝ
አቁመኝ ያለነቀፋ እንዳገለግልህ
ፀጋህን አብዛልኝ /2/

የምስጋና
Amharic
St.Gabriel

Leave a Comment

Scroll to Top