አበርታኝ

35

ጌታ እርዳኝ ምረትህ

ያጠጋጋኝ ወደ ቤትህ
ፍቅርህ ሳበኝ ተማረኩኝ
አዲስ ኪዳን አደረኩኝ

አበርታኝ ጌታዬ አበርታኝ
በፀጋህ በቃልህ አቁመኝ
ህይወቴን ሰጠህ ለአንተ ክብር
አድርገኝ ታማኝ ደቀመዝሙር

በታላቁ መገለጥ እንዳልታበይ
አዘጋጅልኝ የስጋ መውጊያ የሚጐሽመኝ

የለኝም እኔ የምመካበት
በአንተ ነው የማገኝው ብርታት
አበረታኝ ሐይሌን አድስልኝ
ሞገሴ ትምክቴ ሁንልኝ

አላማዬ በቤትህ መጣል ነው
በእድሜዬ አገልግዬ ማለፍ ነው
ጌታ አግዘኝ መንገዱን አሳየኝ
መጠራቴን አምላኬ አፅናልኝ

ከበደሌ ፈፅሞ እጠበኝ
አመፃዬን ከእኔ ውሰድልኝ
መንፈስህን ከእኔ አትውሰድብኝ
በዘመኔ ለአንተ ክብር ልቀኝ

ህይወቴን ላንተ ሰጥቻለው
ካንተ ሌላ አልሻም ብያለሁ
አቤቱ ከንፈሮቼን ክፍት
እንዳበዛ የዝማሬን መስዋት

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top