እግዚአብሔር አምላክ ምህረትን ያሳየህ
በልጁ ደም ደግሞ/2/ የታደገህ
በመንፈስ ቅዱሱ ሁሌ የሚመራህ
አንተ ክቡር ሰው ክቡር ነህ /2/
እንደ እንስሳ ሳይሆን በመልኩ የፈጠረህ
ክብሩንም ሰጥቶህ በገነት ያኖረህ
አንተ ሰው ክቡር ሆይ የፍጥረት የበላይ
ትሑት ሁን ዝቅ በል እርሱ ባንተ እንዲታይ
መንገድህን መርጠህ ከአምላክህ ብትርቅም
እየደጋገምክ ሕጉን ብታፈርስም
ባንተ የሚጨክን አንጀት ስለሌለው
ተመለስ ይልሃል ምህረቱ ብዙ ነው
በጠፋህም ጊዜ ከአምላክ እርቀህ
አሻፈረኝ ብለህ ህግንም ተላልፈህ
ቢሆንም አምላክህ ጨርሶ አልተወህ
የአባትነት ፍቅሩን ካባን አለበሰህ
የህይወትም ዋጋ የተከፈለብህ
ነህ እና አንተ ሰው ጌታ የሞተልህ
ክብርህን በማሰብ እሱን አስከብረው
ድርጊትህን ሁሉ ለክብሩ አድርገው
