አንተ ግን ህያው አንተነህ
እግ/ር ዘመን ሳይሽርህ
አንደጥንቱ ዛቴም ሕያው ነህ
ጉልበትህ ኃይልህ ሳይክድህ
ነገስታት ክብርህን ያያሉ
ጠቢባን ለአንተ ይገዛሉ
ካንተ በላይ ሃያል የለም
ከዘላለም እስከ ዘላለም
1. ትላንት በዛሬ ሲተካ ዛሬም በነገ ቢመካ
የአንተ ካንተ ጋር ይኖራል መች ያልፋል እሱ ይፀናል /2/
የቆመ ያለ ሲመስለው ሰው ለነገ ዛሬ ይመራል
ሁሉ መኖርን ሳይጠላ ሳይፈልግ እራሱን ያጣል /2/
አንተ ግን ህያው አንተነህ
እግ/ር ዘመን ሳይሽርህ
አንደጥንቱ ዛቴም ሕያው ነህ
ጉልበትህ ኃይልህ ሳይክድህ
ነገስታት ክብርህን ያያሉ
ጠቢባን ለአንተ ይገዛሉ
ካንተ በላይ ሃያል የለም
ከዘላለም እስከ ዘላለም
2. ቀናት ወራት ዓመታት ሊቆጠሩ ሊያልፉ ግድ ነው
መኖሪያው ባንተ ያለሆነ ግን እንዲሁ በዋዛ ኃላፊ ነው
እንዲሁ በዋዛ ጠፊ ነው
ከዙፋንህ ላይ ሳትወርድ ሳታረጅ የምትኖር ጌታ
አንተ ብቻ ነህ እግ/ር ዘላለም ክንድህ የበረታ
ዘላለም ኃይልህ የበረታ
አንተ ግን ህያው አንተነህ
እግ/ር ዘመን ሳይሽርህ
አንደጥንቱ ዛቴም ሕያው ነህ
ጉልበትህ ኃይልህ ሳይክድህ
ነገስታት ክብርህን ያያሉ
ጠቢባን ለአንተ ይገዛሉ
ካንተ በላይ ሃያል የለም
ከዘላለም እስከ ዘላለም
3. ስንት አየን የጊዜው ብርቱ ላይዘልቅ በኩራት የኖረ
የአንድ ሰሞን ዜና ሆኖ ዛሬ ተነስቶ የቀረ /2/
አቤት አንተ ግን አንተነህ ጌታ ሳትለወጥ ከቶ
የትላንት ብርቱ አትባልም ዝናህ ማዳንህ ተረስቶ
ዕድሜህም በዕድሜ ተገፍቶ
አንተ ግን ህያው አንተነህ
እግ/ር ዘመን ሳይሽርህ
አንደጥንቱ ዛቴም ሕያው ነህ
ጉልበትህ ኃይልህ ሳይክድህ
ነገስታት ክብርህን ያያሉ
ጠቢባን ለአንተ ይገዛሉ
ካንተ በላይ ሃያል የለም
ከዘላለም እስከ ዘላለም
