እየሱሴ ራራልኝ ለኔ
ጌታ አምላኬ ራራልኝ
ነጥቆ ኣወጣኝ ከሃጢኣት ኩነኔ
በመስቀሉ ሁነልኝ መድህኔ
ተቅበዝባዥ ነበርኩ ባዛኝና አዛኝ
መግቢያ የሌለው ወዳድና ኣጽናኝ
እየሱሴ ግን እራራልኝና
ከጭንቅ አወጣኝ እጄን ያዘና
የህይወት እስትንፋስ ከእኔ ለማለፍ
ገደል አፍ ሆና ስትንደፋደፍ
በፍቅሩ ጋሻ እየሱስ አቅፎ
አዳነኝ ይኸው ያ ሁሉ አልፎ
አፍቃሪን አጥቶ ስጋዬ ኣምጾ
በአካሌ ውስጥ ጣኦትን ቀርጾ
ሞትን ሊከተል መንገዱን ስቶ
እየሱስ መለሰው ሕይወትን ሰጥቶ
