ኢየሱስ ያድናል

218

ኢየሱስ ኢየሱስ ያድናል/2/
ኢየሱስ ኢየሱስ ያድናል/2/
መዳን መዳን መዳን በማንም ዘንድ የለም/2/
መዳን በሌላ ዘንድ የለም

ኢየሱስ ያድናል እያልኩ አወራለሁ
መድኃኒት መሁኑን ለዓለም አውጃለሁ
የማዳኑ ምስጢር እጅግ የረቀቀ
ለሰው የማይቻል ከኣይምሮ የላቀ/2/

ኢየሱስ ኢየሱስ ኢየሱስ ያድናል
እራሱን በመስጠት ለዓለም ቤዛ ሆኗል
ስሙ የሚጣፍጥ ከማር ከወተት
ዘላለም ሚነግስ አዳኝ ነው ኢየሱስ /2/

እናንተ ደካሞች ሸክም የከበዳችሁ
ኑ ወደ ኢየሱስ ይሰጣል ሕይወት
ቀንበሩ ልዝብ ነው ሸክሙ ቀላል
የትሁቶች ትሁት የዋህ ነው በእውነት /2/

የድካማችሁን ዋጋ ላያጠግብ
ከቶ አትፈልጉ ጊዜያዊውን ክብር
ክርስቶስ ነው መንገድ እውነትና ሕይወት/2/
ብትሹ እርካታ ለነፍሳችሁ ዕረፍት

እኔስ ሾሜዋለሁ ኢየሱስን በኔ
በቀሪው ሕይወቴ ለመጪው ዘመኔ
ኢየስስ ኢየሱስ ኢየሱስ ነው ለኔ
የመዳን መገኛ ለእኔ ሕይወቴ /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top