እረዳቴ ኢየሱስ

24

አይዞህ ባይ የለኝም ችግሬን ተካፋይ
ደስ ሲለኝ አጫዋች ሲከፋኝ አባባይ
በማለት እራሴን ዘወትር ሳስጨንቅ
አንድ እረዳት አገኘው ብቻዬን ስማቅቅ

አለምን ሳደንቃት ስከተላት ኖሬ
መች ተቃለለልኝ በዛ እንጂ ችግሬ
ክርስቶስ እረዳቴን ፈፅሞ እረስቼ
ምኖር መስሎኝ ነበር በአለም ተደስቼ

እረዳቴ ኢየሱስ ዘለኣለም መድህኔ
ከእንግዲህ አልሄድም ከኣንተ ተነጥዬ

ከእንግዲስ በቃኝ መድህን አግኝቻለሁ
ክርስቶስን ይዤ አለምን ንቂያለሁ
እርቄ እንዳልሄድ አንተን ጥዬ ኢየሱስ
ሐሳቤን ስራዬን ባርክና ቀድስ

ከእንግዲህ የአንተ ነኝ እስከመጨረሻ
ተከላካይ የለኝ ያላንተማ ጋሻ
ወዳንተ እስክመጣ ክቡር ቃልህ ጠፍቶብኝ
እንዳላሳዝንህ አምላክ ሆይ ጠብቀኝ

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top