ሁሉም እችላለሁ ቅሬታ አይገባኝም
ከአንቺ መለየት ግን ከቶ አይሆንልኝም
ከአንቺ ጋር መኖር ነው ለእኔ የሚረዳኝ
በእንባ እንዳልታጠብ ትካዜ እንዳይገባኝ
እባክሽ ማርያም ሆይ ፊትሽን ልመልከት
ህይወት እንዲሰጠኝ የፍቅርሽ በረከት
ከምወድሽ ከኣንቺ ከተለየሁማ
እንዴት አልፈዋለው የንሮን ጨለማ
ተለይቼሽ መዋል እንደማልችል ስታውቂ
እባክሽ ማርያም ሆይ ከልቤ አትራቂ
በዚች አለም ውስጥ ሆኜ ስደተኛ
ማርያምን አገኘው ለልቤ ጓደኛ
በጥርስሽ ፈገግታ በድምፅሽ ተማርኮ
ማርያም ከአንቺ ሌላ ልቤ አይሻም ከቶ
