እናትን ሰጥቶናል

180

የሃዘናችን ተካፋይ የችግራችን ደራሽ
በሞት ጥላም ቢሆን ይፈጥናል ከለላሽ
ከፍጥረታት ሁሉ ፍፁም ተለይተሻል
ኦ ማርያም እናት ሆይ አምላክን ወልደሻል /2/

እንዲሁ አፍቅሮናል እናትን ሰጥቶናል
የፍቅሩንም ሚስጥር በእርሷ አከናውኗል
ከኢምንት አንስቶ ክብርን አጐናጽፎናል
እግዚያብሔር አምላክ እናትን ሰጥቶናል

ሐጥያታችንም እጅግ በጣም በዝቶ
ፈጣሪ አምላካችን በጣም አስቆጥቶ
መዓቱን ሲያወርድ ፈጥነሸ ተማፀኚው
ለእኛ ለደካሞች ምህረትን ለምኚው /2/

የፍቅርንም ጣእም ከእኛ ሳይሸሽገው
ለፍጥረትም ሁሉ ፍቅሩን ሳይነፍገው
በእናቱ በማርያም በገሃድ ገልጾታል
ክብርና አምልኮ ስግደት ይገባዋል /2/

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top