1. ዝም ልል አልችልም ፍቅሩ ግድ ይለኛል
ያረገውን ነገር መስክሪው ይለኛል
እንደባህር ዓሳ እንደ ወንዝ አሸዋ
እያየሁ ሲበዛ የሱ ድንቅ ስራ
አዝ፦ እኔም ልነሣና ድንቁን ላውራ
የጌታ የአምላኬን ሥራ
ልሂድና ልገኝ ከመቅደሱ
ምስጋናዬን ልስጠው ለሱ ለሱ ለሱ
2. በፍቅሩ ጠብቆ ሁሉን እየቸረኝ
ደግፎ ደጋግፎ ሁሉን ሲያሳልፈኝ
ታሪኬን ለውጦ ሰዲስ ሰው አድርጎኝ
እንዴት ዝም እላለው እኔም አያስችለኝ
አዝ፦ እኔም ልነሣና ድንቁን ላውራ
የጌታ የአምላኬን ሥራ
ልሂድና ልገኝ ከመቅደሱ
ምስጋናዬን ልስጠው ለሱ ለሱ ለሱ
3. የጨለመው ሰማይ አየሁት ሲበራ
ወጀቡ ጸጥ ሲል በሱ ድንቅ ስራ
ለዚህ ሃያል አምላክ ምስጋና ይድረሰው
እንዴት ዝም እላለው ታምርን እያው
አዝ፦ እኔም ልነሣና ድንቁን ላውራ
የጌታ የአምላኬን ሥራ
ልሂድና ልገኝ ከመቅደሱ
ምስጋናዬን ልስጠው ለሱ ለሱ ለሱ
