እኔ የማምነው አንድ ነገር

113

እኔ የማምነው አንድ ነገር
ከእርሱ ብቻ ቃል ይነገር
ያደርጋል ያለውን ነገር

ጊዜው ይርዘም እንጂ ያለውን ያደርጋል
ጌታ ሰው አይደለም መቼ ቃሉን ያጥፋል
በትዕግት ቆይታ በፀሎት በእርጋታ
በእርግጥ መልስ ያገኛል ከላይኛው ጌታ

አሜን ይሁንልቃ ጌታ ያሰበልኝ
በህይወቴ ይፈፀም እርሱ ያየልኝ
አይቸኩልም ጌታ ደግሞም አይዘገይም
ቀስ እያለ ቢሄድ ማንም አይቀድመውም
ነገርን በጊዜው ውብ ኣድርጐ ይሰራል
እርሱ አዋቂ ነው በማን ይታረማል

በለስ የጠበቀ ፍሬዋን ይበላል
ጌታን የታመነ በርግጥም ይከብራል
እኔ እጠብቃለሁ አምላኬን ታምኜ
ሳልነዋወጥ በስፍራዬ ሁኜ

እኔ ለምጃለሁ ብዙ ብዙ ነገር
በእምነት ተቀብዬ እግዚኣብሔር ሲናገር
ሲፈፀም በህይወቴ ተከናውኖ ሳየው
ተናግሮ የሚያደርግ ጌታ ብቻ ነው

የትንሳኤ

Leave a Comment

Scroll to Top