እግዚትነ ማርያም የትህትና ቤት
የፍቅር ታቦት ነሽ የእኛ እመቤት
ፀጋ የሞላሽ ተብላ ስትጠራ
ትዕቢት አልያዘችም አለፈች ሳትኮራ
መሲህ እንድትወልድ ከአምላክ ስትመረጥ
ኩራት አልነበረም በእርሷ ውስጥ
ጭራሽ ያስገርማል ትህትናዋ
ወደ ኤልሳቤጥ ሄደች ይዛ ፍቅሯን
መገልገል ሲገባት አገልጋይ መሆኗን
ያሳየናል ውበት ትህትናዋን
የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ
እንዴት ይሆንልኛል ኧረ እንዴት
ብላ ተመለሰች ንፅህት እመቤቷን
እጅግ አከበረቻት ቅድስት ማርያምን
ውስጧ ያለው ጽንሱ ዮሐንስ
በማህፀኗ ዘለላ ማርያም ስትደርስ
እግዚትነ ማርያም ናት የተባረከች
ድንግልም እናት እመቤት የሆነች
