እግዚብሔር ለዚህ ቀን ስላደረሳችሁ
እናተ ሙሽሮች እንኳን ደስ አላችሁ
ጌታ ኢየሱስ ይንገስ በመሐከላችሁ
ዛሬ እንደጀመረ እስከ ፈፃሜያችሁ
አሜን/6/
የሕይወት ውሃ ምንጭ ኢየሱስ ነውና
ይሆናል ፍቅራችሁ ዘለአለም የፀና
በድርቅ ወራትና በጥማት ጊዜያችሁ
ኢየሱስን ጥሩት እንዲያፈልቅላችሁ
ፍቅር ሲመነምን ጥላቻ ሲመጣ
ኢየሱስን ጥሩት የሰላሙን ጌታ
ሰዎች እንዳይገቡ በመሐከላችሁ
ጌታ ኢየሱስ ብቻ ይሁን ሚዛናችሁ
የፍቅር ጌታ ነው ስለፍቅር ያውቃል
እርሱ ጓዳኛችሁ ከሆነ ይበቃል
ዘወትር ባዶ ነው ውጤቱ በኋላ
ጌታ ካልተገኘ ይሆናል አተላ
