እግዚአብሔር ሓያል ነው

284

ክበር በማለት ፋንታ እኔ ዝም አልልም
በመመስከር ፋንታ ከቶ አፌን አልዘጋም
እጅህን በብዙ አይቻለሁና
ሁሌ አከብርሀለሁ ጌታዬ ገናና
አምላኬ ገናና እግዚአብሔር ገናና /2/

እስኪ ክበር ክበር ልበል እስኪ
እሰኪ ክበር ክበር ልበል እሰኪ
እስኪ ንገስ ንገስ ልበል እሰኪ
እሰኪ ክበር ንገስ ልበል እስኪ

ከፍ ካለው ሰማይ ከከፍታ
እንዳንተ የሚሆን የለም ጌታ

ከምድር ሃያላን ነገስታትም ቢሆን
የትም አይገኝም እንዳንተ የሚሆን /2/
የሆታ ድምፅ የእልልታ አምጡለታ ለዚህ ጌታ /2/
አቅም ያለው የበረታ ያመስግነው ድንቁን ጌታ /2/
እግዚአብሔር ሃያል ነው /3/ ከፍ ከፍ እናርገው
ከፍ በል የኔ ጌታ ከፍ በል ከፍ በል
አቀርባለሁኝ ምስጋና ከዚህ በላይ ምን ልበል /2/

አንደበቶች ሁሉ አፍልቁ ምስጋና
ለልዑል እግዚአብሔር ይገባዋልና
ፀጋውን በሙላት ሁሌ ለሚሰጠን
ባርኮቱን በብዛት ላትረፈረፈልን

የማርያም

Leave a Comment

Scroll to Top